3901 items (2338 unread) in 6 feeds
Amharic News የአማርኛ ዜና
(1818 unread)
Washington DC (Ethiopian)
(520 unread)
አዲስ አበቤው ተመዝግቦ የከፈለበትን የኮንዶሚንየም ቤት ተነጥቆ
እነስዩም በረደድ ሊያከራዩት መሆኑ ተደረሰበት
በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን አገር አቀፍ ምርጫ ምክንያት በማድረግ ቅስቀሳ ሲደረግ የአብዛኛውን ወገን ድጋፍ ለማግኘት ይረዳኛል ብሎ ያሰበው ወያኔ ኢህአዴግ ላታለያነት ተጠቅሞበት የነበረውን «የመኖሪያ ቤት ችግር እቀርፋለሁ» የሚለው ስብከቱ በምርጫ መሸነፉን ካወቀ ወዲህ ቃሉን ለማጠፍ መገደዱንና አሁንም የቅድሚያ ክፍያቸውን ለከፈሉ ዜጎች ሳይሰጥ ለራሱ መታያና የፕሮፓጋንዳ ትርፍ መሰብሰቢያ ሊያደርገው መሆኑን ምንጮቻችን ዘገቡ
በወያኔ ኢህአዴግ አፍቃሪነታቸውና ሙዋቹን ክንፈ ገብረ መድህንን የተከካው የደህንነት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው የስጋ ዘመድ የሆነው ስዩም በረደድ እና በተቃያያሪ አመሉ የሚታወቀው ሙሉጌታ አስራተካሳ የሚመራው የሚሊኒየም አከባበር ብሄራዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ድሃ ህዝብ ስም የተሰሩ የኮንዶምኒየም ቤቶችን ከግፈኞች እና ከአምባገነን ገዳዮች ጋር አጨብጭቦ ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን እንግዶች መቀበያና ማስተናገጃ ሊያደርገው መሆኑን ታማኝ ውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ ምንጮቻችን ዘግበዋል
ለአዲስ አበባ መስተዳድርና ለአዲስ አበባ የቤቶች ኤጀንሲ ቅርብ የሆኑት እነዚሁ ታማኝ ውስጥ አዋቂዎች በወያኔ ኢህአዴግ የግድያ ትእዛዝ በግፍ ደማቸው በፈሰሰ ወገኖች መቃብር ላይ ለመረማመድ እና ለመጨፈር የተጋበዙ እንዲያርፉበት ተብሎ ከእለት ጉሮሮው እየቀነሰ በችግር ተቆራምዶ ቅድሚያ ክፍያ የከፈለበትን የኮንዶሚንየም ቤት የሚያጣው የአዲስ አበባ ነዋሪ «ለምን᐀» ብሎ ጥያቄ እንዳያነሳ ቤቱ የሚሰጠው በእጣ ስለሆነ እጣው አልወጣም ጥሪ እስኪደረግላችሁ ተጠባበቁ የሚል መልስ እንዲሰጥ በቤቶች ኤጀንሲ በኩል መወሰኑን እናውቃለን ሲሉ አስረድተዋል
እየገደሉ እያፈኑ እና በጅምላ እያሰሩ የስልጣን እድሜውን አራዝሞ መኖር ለመረጠ ፋሽስት ጋር ተባባሪ ሆኖ በድሃው ህዝብ ላይ መደለል አሳዛኝ ነው የሚሉ የጉዳዩ ተመልካቾች ነዋሪውም ቢሆን እኮ የወያኔ አጨብጫቢዎችና አሸርጋጆች የሚያከብሩት ሚሊኒየም አድማቂ ሳይሆን በግፍ የተሰዉ የዲሞክራሲ ሰማእታት መንፈስ እንዳይፋረደው ራሱን ቢያገልም እንደ ማንኛውም አዲስ አመት በአዲስ ቤት መኖር አይጠላበትም ግን የኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናት ከህዝብ ጥቅም የራሳቸው ጥቅም ስለሚበልጥባቸው ይህን እርምጃ ለመውሰድ ተገድደዋል በማለት መናገራቸው በዘገባው ተመልክቶዋል
በበላይነት ስዩም መስፍን የሚመሩትና በእነስዩም በረደድ እና ሙሉጌታ አስራተ ናሳ አማንኝነት ሊካሄድ የታቀደው የወያኔ ሚሊኒየም በአል ለማክበር ይገኛሉ ከእኛ ጋር ያጨበጭባሉ ተብለው የተገመቱት ወገኖች ህሊና ሳይኖራቸው ቀርቶ ቢመጡ ሊያርፉበት የሚችሉትን ቤት ያለ ህዝብ ፍላጎት በአዲስ አበባ ህዝብ ትከሻ ላይ መቀመጥ የመረጡት የሞግዚቱ አስተዳደር ብርሃነ ዴሬሳ ፊርማ ወጪ የተደረገ ደብዳቤ ለከተማው ቤቶች ኤጀንሲ እንዲደርስ መደረጉ ታውቆዋል
በዚህም መሰረት ይህ ኢህአዴጋውያን የተጠራቀሙበት ኮሚነ የኮንዶሚኒየም ሕንፃዎችን ለመጠቀም ተፈቅዶለታል ሲሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል
በዚሁ የወያኔ ሚሊኒየም በዓል እስከ 300 ሺህ የሚገመቱ እንግዶች ይመጣሉ የሚሉት እነስዩም በረደድ የግንቦቱን ምርጫ ተከትሎ ወያኔ ሰላማዊ ዜጎችን ሲገድል በእንባ እየተራጩ ወገኔ አለቀ አስጥሉልኝ ብለው ምእራባውያንና አውሮፓውያንን የተማጸኑ ዜጎች በወቅቱ የተቀረጸ ምስላቸው የተቃውሞ ድበጻቸውን ካሰሙበት አገር ከሚገኝ ኤምባሲ በወያኔ ኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚዎቸር ተቀነባብሮ አዲስ አበባ ለሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስነር መስሪያቤት መላኩንና የሚኒስነር መስሪያቤቱ የተለያዩ ክፍሎችና ዳይሬክቶሬቶች ውስጥ ያሉ የኢህአዴግ ታማኝ አገልጋዮች «እገሌ ፤ እገሌ» እያሉ በመምረጥ ላይ መሆናቸው ለማወቅተችሎዋል
ይህ የሚያገለግለው የሰው ዘር ማየት ያስጠላው ወያኔ ኢህአዴግ በአል ብለው የሚመጡ እንግዶችን ከቦሌ አየር ማረፊያ የእግረ ሙቅ በማጥለቅ አቀባበል ሊያደርግላቸው በማሰቡ መሆኑን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስራ የበዛባቸው የደህንነት ተቁዋሙ ባልደረቦች መናገራቸው በዘገባው ተመልክቶዋል
ለበዓሉ የሚመጡትን እንግዶች ከሆቴሎች ሌላ ሌሎች ማረፊያ ቦታዎችን ለማመቻቸት ከሚያስችለው ዝግጅት አንዱ የሆነውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝግቦና ገንዘቡን ከፍሎ እረከባለሁ በማለት ከሚጠባበቀው ህዝብ በመንጠቅ ለመስጠት ስምምነት ላይ መደረሱን የሰሙ ወገኖች ጥራት የጎደለው እና በመሰነጣጠቅ ገና ከጅምሩ የማስመሰያ ግንባታ እንደነበረ ህዝቡ አውቆታል ከዚሁ ብሶ በሸፍጥ ለሌላ በማዛወር ገንዘብ ለማግበስበስ መሞከር አልጠግብ ባይነት ነው ሲሉ የወያኔ ኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናትን በሆዳቸው መሸነፍ አስመልክተው መተቸታቸው በዘገባው ተመልክቶዋል
እነስዩም በረደድ በበዓሉ ዋዜማ ዓመቱን በመሉ ሊመጡ የሚችሉ እንግዶችን በአዲስ አበባ ከተማ በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ኮንዶሚንየም ቤቶችውስጥ እንዲያርፉ በማድረግ የገቢ ምንጭ የሚሆኑበት መንገድ ተሰልቶ ስለሚገኘው ትርፍ ግምታዊ ስሌት የሚያሰላ ቡድን እንዶቁዋቁዋም ማድረጋቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ንን ዘገባ እያጠናቀርን ባለንበት ወቅት በተገኛ ተመሳሳይ የምንጮቻችችን ዘገባ በኮንዶሚኒየም ቤቶች ከሚያርፉ እንግዶች ሌላ በእነሱም መካከል ልዩነት በመፍጠር በኮንዶሚኒየም ለመቆየት የሚጠየቁት ክፍያ መክፈል ካልቻሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት ተማሪዎች ትምህርት እንዲያቆሙ ማድረግ አስቸጋሪ ነው ተብሎ ቢታሰብም ማደሪያ ክፍሎቻቸውን እንዲለቁ እና ዩኒቨርስቲዎች የመኝታ አገልግሎታቸውን ለእንግዳ ማረፊያ እንዲከራይ ሀሳብ መቅረቡን ለማወቅ ተችሎዋል
ይህ ሃሳብ ሁለት ዋና ዋና የተባሉ ጥያዎችን አስነስተው ነበር ያሉት ምንጮቻችን አንዱ የዩኒቨርስቲ መኝታዎች የሚያስገኙትን ገቢ በባለቤትነት የሚወስደው ማንነው᐀ የሚለው ሲሆን ሁለተኛው የክፍለሃገር ተማሪዎችን በተመለከተ ወዴት ማዘዋወር ይቻላል᐀ የሚለውን ከሌሎች ጥያቄዎች ጋር አዛምዶ መልስ ለመፈለግ ጉዳዩ ይጠና መባሉን ከታማኝ ውስጥ አዋቂ ለማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ዘግበዋል
በግቦት ወር 1997 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በማግኘት ከንቲባው እንዲሆኑለት ህዝቡ የመረጣቸውን ከንቲባ ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ወህኒ እንሰዲገቡ ያደረገው ወያኔ ኢህአዴግ ያለ ህዝብ ድጋፍ የሞግዚት አስተዳደር አድርጎ የመደባቸው ብርሃኑ ዴሬሳ እያወቁ የፍርደስ ቤት ውሳኔ መሻራቸው አዲስ አበባ የሚገኙ ምንጮች አስታወቁ
በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የከተማ ትርፍ ቤቶችን እንዲወረሱ ያደረገው የየካቲት 67 አዋጅ መሰረት ለረጅም ዓመታት የቀበሌ ናቸው በማለት ሲያከራክር የነበረውን ሁለት መኖሪያ ቤቶች በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ ብርሃኑ ዴሬሳና የበታች ሹማምንቶቻው መሻራቸው አነጋጋ መሆኑ ታዉቆዋል
አምና በሐምሌ ወር 1998 ዓ.ም. ለህጋዊ ወራሾች ይመለስ ሲል የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማው ሽሮታል ያሉት ምንጮች የወራሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ መሰረዝ በክፍለከተማው ቀበሌ 19/20 የሚገኙ የቤት ቁጥራቸው 130 እና 131 የሆኑ በ3.000 ካሬ ሜትር ላይ የተሰሩ ቤቶች በውርስ የተላለፈላቸው እና የቤቶቹ ባለቤት ስለመሆናቸውም የሚያረጋግጥ የማረጋገጫ ደብተር ያላቸው ወራሽ ከፍርድ ቤት የተወሰነላቸውን ውሳኔ ለመሻር የሚያበቃ ስልጣን እንደሌለው የህግ ባለሙያዎች መናገራቸውን ጨምረው አስረድተዋል
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቤቶቹ ላይ የባለቤትነት መብት ሳይኖረው በማከራየት ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱ እንዳለሆኖ ቤቶቹን እንዲያስረክብ ቢጠየቅም እምቢ ብሎዋል
ከሳሽ ክሱን ሲመሰርቱ ካቀረቧቸው ማስረጃ መካከል የቤቶቹ ባለቤት ስለመሆናቸውና በውርስ መተላለፋቸውን የሚያስረዳ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1985 ዓም የተሰጣቸውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ፍ/ቤቱ በማስረጃነት በመያዝ ፍ/ቤቱ ቤቶቹን ለከሳሽ እንዲያስረክቡ በ17/11/98 ዓ.ም. በመወሰን ለክፍለ ከተማው ያስታውቃል ፡፡
ይሁን እንጂ የፍ/ባለመብት ውሣኔው ተግባራዊ እንዳልሆነላቸው በመግለፅ ፍ/ቤቱ እንዲያስፈፅምላቸው በጠየቁት መሠረት በ10/2/99 ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
ቤቶቹ በፍርድ ባለእዳዎች ተይዘው ከሆነ በማስለቀቅ፣ ተቆልፈው ከሆነ በጥንቃቄ በመስበር ለፍፍርድ ባለመብት እንዲተላለፉ ለፖሊስ በትዕዛዝ ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ይህም ተግባራዊ እንዳይሆን ክፍለ ከተማው ያግዳል የዚህ ምክንየት ደግሞ ኢህአዴግ ታማኝ ባለሙዋሎች ጌቶቻቸውን የሚያስደስት የሚመስላቸው ህዝብን በማስለቀሳቸው እንደሆነ ስለሚያምኑ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጭራሹኑ ፍርድ ቤት የፃፈው ደብዳቤ ተቀባይነት እንደማይኖረው ለፍርድ ባለመብት እንዲያውቁት አደረገ፡፡
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ባለስልጣን ለክፍለ ከተማው በፃፈው ደብዳቤ ቤቶቹ ኪራይ የሚከፈልባቸው የመንግስት ቤቶች መሆናቸውን የሚያስረዳ መረጃ በማዕከል እንዳለ መግለፁን ክፍለ ከተማለው ደግሞ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን በሕገ ወጥ መንገድ የተሰጠን የበት ባለቤትነት ሥልጣን በሕገወጥ መንገድ የተሰጠን የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር መሠረዝ የሚችል ስልጣን ስላለው የፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኙ ባለመብቶች በእጃቸው የሚገኘውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እንዲመልሱ መጠየቁ የአስተዳደር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን ነጻ ነው እየተባለ የሚለፈፍለት ፍርድ ቤት በኢህዴግ ታማኝ አገልጋዮች የእጅ መዳፈ ላይ ያለ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ አንድ የህግ ባለሙያ መናገራቸው ታውቆዋል
ይህ ሁሉ ሲሆን በህዝብ ሳይመረጡ የተሾሙት ብርሃኑ ዴሬሳና ካቢኔያቸው ስለጉዳዩ እያወቁ ዝምታን መምረጣቸው የራሳቸውና የአባላቶቻቸው ጥቅም እስንልተነካ ድረስ ስለሌላው የህብረተሰብ ክፍል ምንም ደንታ የሌላቸው መሆኑን አስመስክሮዋል
በታቃዋሚነታቸው ስመጥር የሆኑ በሐገር ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች እንደ ጠላት የሚታዩበትና ሕልውናቸው በስጋትና በአደጋ ላይ እየወደቀ የመምጣቱን ጉዳይ ከቀን ቀን ድርጊቶች ገሐድ እያወጡት በሚጉኙበት ሒደት ላይ እንገኛለን፡፡
በመንግስት ከፍተኛ የኃላፊነት የሥልጣን እርከን የነበሩና ታማኝነታቸው አጠራጥሮ ከነበሩበት ቦታ ዝቅ ተደርገው ከተቀመጡት ግለሰቦች ጀምሮ ሕወሓትንና በኋላም ኢህአዴግን ትናንትም ሆነ ዛሬ በመቃወም በአደባባይ እስከማውገዝ በደረሱ ግለሰቦች ሕይወት ዙሪያ የሚፈፀመው ወንጀል አሳዛኝና አስገራሚ ከመሆን አልፎ የተፈፀመባቸው የግድያ ወንጀልም ሆነ የአሟሟታቸው ጉዳይ ሁኔታዎች ከሚጠቁሙት ውጭ ይህ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡
ይባስ ብለው « ግለሰቡ እራሱን በራሱ ገደለ፡፡» ደመኛ ገደለው «ወንጀል ፈፅሞ ሲያመልጥ ተገደለ» የሚሉ እና ሌላ ሌላም ሽፋን ሲሰጣቸው ይስተዋላል፡፡ ይህ አባባል የግድያውን ስልታዊነት የሚጠቁም እንደሆነ አንዳንድ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
በሰሜን ጎንደር የተገደለው ወጣት የሽምቅ ውጊያ መሪ አገዳደሉ የክልሉ ባለስልጣኖች እንደሚሉት «በደመኛ» ሳይሆን ሆን ተብሎ በተጠነሰሰ የባለጊዜዎች ሴራ እንደተገደለ አብዛኛው የክልሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
ቀኑ ሐሙስ ነው ወሩ መፊቢት 5 ቀን ከዛሬ 14 አመት በፊት 1985 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡45 አካባቢ በአድርቃይ ወረዳ በዛሪማ ከተማ አሳዛኝ የግድያ ወንጀል በወጣቱ የጦር መሪ በኪዳነ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር ላይ ተፈፀመ፡፡ በኪዳነማርያም ላይ የተፈፀመውን ግድያ አሰቃቂ የሚያደርገው በበርካታ ሽማግሌዎች ልመና በምህረት ከገባ ከአምስት ወር በኋላ በታዩት ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በተሰላ ደባ የሞት ሰላባ መሆኑ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ኪዳነማርያምና የተወሰኑ ጓደኞቹ በምህረት እንዲገቡ የመንግስት ባለስልጣኖች ሽማግሌዎችን በመላክ ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ በኋላ ከሃያ የማያንሱ ካህናትና ሸማግሌዎች የየአድባራቱን መስቀል በመያዝ አርማዛሊ ከተባለ በረሐ ዳር በአርማዶጋ ውስጥ ከሚገኙት ከእነ ኪዳነማርያም ጋር ጥር 10/1985 ዓም በመገናኘት ድርድር ተጀመረ፡፡
ብዙም ሳይቆዩ ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡ በዚህን ጊዜ ኪዳነና ጓደኞቹ ጦሩን ሰብስበው «በምህረት ልንገባ ነው» በማለት በተናገሩ ጊዜ ተቃውሞ ቢያጋጥማቸው ሁኔታውን ለማሳመን ሞክረው ነበር፡፡ በመጨረሻም ጦሩ «እንደሚገሏችሁ አትጠራጠሩ፡፡ እኛ ግን አንገባም፣ ደህና ሁኑ» በማለት ነበር የተሰናበታቸው ፡፡ አንዳንድ የጦሩ አባላት በኪዳነ ማርያም እግር እየወደቁ «ማማዬ ምነው ጥለኸን አትሂድ እንጂ᐀» እያሉ ቢለምኑትም የዋህ እንደሆነ የሚነገርለት ኪዳነማርያም ልቡ ጨክኖ « የሐገሬውን ሸማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶችን አላሳፍርም፣ አላሳዝንም እናንተ እዘኑ እንጂ» በማለት ነበር እንደ እናት የሚያዩትንና እንደ ልጅ የሚያየውን ጦሩን ጥሎ በምህረት የገባው፡፡
ኪዳነና ጓደኞቹ በተጠቀሰው ቀን በሙሉ ምህረት በዘሪማ ከተማ ቢገቡም፣ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ በመገኘት «በግል ያጠፋሁት ጥፋት ካለና የገደልኩት ካለ በሽማግሌ አማካኝነት የተፈረደብኝን እከፍላለሁ» በማለት ቃል ገብቷል፡፡ ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ቃል እንደገቡ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን በክልሉ ከሕወሓት ጋርና በኋላም ከኢህአዴግ በመወገናቸው ሲዋጓቸው የነበሩና የቤተሰቦቻቸውን ሐብት ንብረት ያወደሙና የነጠቁ ታጣቂዎች በአሁን ወቅት በስልጣን ላይ በመሆናቸው በኪዳነ ጓደኛ ላይ የማቁሰል አደጋ በማድረስና በማሰር ከፍተኛ በደልን በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ ሲረዳ ሐዘን ገብቶት እንደነበርና «እኔን አምነው እንዲህ ተሰቃዩ» በማለት ይቆጭ እንደነበርና እርሱም ሆነ ሌሎች ጓደኞቹ የወቅቱን ፖለቲካ ሲየጤኑትና ነገሮችን ሲመለከቷቸው የከተማው ኑሮ አልዋጥ ብሏቸው እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ ይናገራሉ፡፡
ኪዳነ ማርያም ከቤቱ በር ላይ ሲገደል በቅርብ የነበሩት መጠጥ በመሸጥ የሚተዳደሩት ወ/ሮ እንባ እየተናነቃቸው «ከእርሱ ጋር ሙሉ ምህረት ተደርጐለት በገባው ጉዋደኛው መታሰር ያበሳጨው ስለነበር ወዲያ ወዲህ ብሎ ነገሮችን ካስተካከለ በኋላ ሐሙስ ግንቦት 5 ቀን ጠዋት ጀምሮ ከሳሾቹንና ሽማግሌዎችን በመያዝ እስከ ሰባት ሰዓት እርቅ ሲያደርግ ውሎ በመጨረሻ ተሳካለት፡፡
ያን ቀን እቤት ሲገባ ደስተኛ ነበር፡፡ ምሳ በልቶ ወደ አድርቃይ ጉዋደኛውን ለማስፈታት እንደሚሄድ ነግሮኝ ከቤት ወጣ አሉ እንባቸውን አብሰው የዚያን ግዜውን ድርጊት አስታወሱና ቀጠሉ
«ከዚያም ዘጠኝ ሰዓት ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ከሐገሩ ሰዎችና ከአድርቃይ ምክር ቤት አባል ጋር ተመልሶ መጣ፡፡ ምነው ብዬ ብጠይቀው አንድ የሚያስጨርሰው ጉዳይ ስላለ ጉዞውን መሰረዙን ከነገረኝ በኋላ በጣም ሙቀት ስለነበር ሁሉም እበር ላይ ተቀምጠው ጠላ በማስመጣትና በመጠጣት ሲጫወቱ አመሹ፡፡ ኪዳነ አይጠጣም፣ ብቻ በእርቁ መደሰቱን ለመጣው ሁሉ ይናገራል፡፡ ሁለት ሰዓት ሲል ወደ ቤት ውስጥ ገቡ ትንሽ እንደቆዩም እራት አቅርቤላቸው በሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ስለሄዱ የቀሩ