3554 items (1991 unread) in 6 feeds
Amharic News የአማርኛ ዜና
(1475 unread)
Washington DC (Ethiopian)
(516 unread)
አዲስ አበቤው ተመዝግቦ የከፈለበትን የኮንዶሚንየም ቤት ተነጥቆ
እነስዩም በረደድ ሊያከራዩት መሆኑ ተደረሰበት
በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን አገር አቀፍ ምርጫ ምክንያት በማድረግ ቅስቀሳ ሲደረግ የአብዛኛውን ወገን ድጋፍ ለማግኘት ይረዳኛል ብሎ ያሰበው ወያኔ ኢህአዴግ ላታለያነት ተጠቅሞበት የነበረውን «የመኖሪያ ቤት ችግር እቀርፋለሁ» የሚለው ስብከቱ በምርጫ መሸነፉን ካወቀ ወዲህ ቃሉን ለማጠፍ መገደዱንና አሁንም የቅድሚያ ክፍያቸውን ለከፈሉ ዜጎች ሳይሰጥ ለራሱ መታያና የፕሮፓጋንዳ ትርፍ መሰብሰቢያ ሊያደርገው መሆኑን ምንጮቻችን ዘገቡ
በወያኔ ኢህአዴግ አፍቃሪነታቸውና ሙዋቹን ክንፈ ገብረ መድህንን የተከካው የደህንነት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው የስጋ ዘመድ የሆነው ስዩም በረደድ እና በተቃያያሪ አመሉ የሚታወቀው ሙሉጌታ አስራተካሳ የሚመራው የሚሊኒየም አከባበር ብሄራዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ድሃ ህዝብ ስም የተሰሩ የኮንዶምኒየም ቤቶችን ከግፈኞች እና ከአምባገነን ገዳዮች ጋር አጨብጭቦ ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን እንግዶች መቀበያና ማስተናገጃ ሊያደርገው መሆኑን ታማኝ ውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ ምንጮቻችን ዘግበዋል
ለአዲስ አበባ መስተዳድርና ለአዲስ አበባ የቤቶች ኤጀንሲ ቅርብ የሆኑት እነዚሁ ታማኝ ውስጥ አዋቂዎች በወያኔ ኢህአዴግ የግድያ ትእዛዝ በግፍ ደማቸው በፈሰሰ ወገኖች መቃብር ላይ ለመረማመድ እና ለመጨፈር የተጋበዙ እንዲያርፉበት ተብሎ ከእለት ጉሮሮው እየቀነሰ በችግር ተቆራምዶ ቅድሚያ ክፍያ የከፈለበትን የኮንዶሚንየም ቤት የሚያጣው የአዲስ አበባ ነዋሪ «ለምን᐀» ብሎ ጥያቄ እንዳያነሳ ቤቱ የሚሰጠው በእጣ ስለሆነ እጣው አልወጣም ጥሪ እስኪደረግላችሁ ተጠባበቁ የሚል መልስ እንዲሰጥ በቤቶች ኤጀንሲ በኩል መወሰኑን እናውቃለን ሲሉ አስረድተዋል
እየገደሉ እያፈኑ እና በጅምላ እያሰሩ የስልጣን እድሜውን አራዝሞ መኖር ለመረጠ ፋሽስት ጋር ተባባሪ ሆኖ በድሃው ህዝብ ላይ መደለል አሳዛኝ ነው የሚሉ የጉዳዩ ተመልካቾች ነዋሪውም ቢሆን እኮ የወያኔ አጨብጫቢዎችና አሸርጋጆች የሚያከብሩት ሚሊኒየም አድማቂ ሳይሆን በግፍ የተሰዉ የዲሞክራሲ ሰማእታት መንፈስ እንዳይፋረደው ራሱን ቢያገልም እንደ ማንኛውም አዲስ አመት በአዲስ ቤት መኖር አይጠላበትም ግን የኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናት ከህዝብ ጥቅም የራሳቸው ጥቅም ስለሚበልጥባቸው ይህን እርምጃ ለመውሰድ ተገድደዋል በማለት መናገራቸው በዘገባው ተመልክቶዋል
በበላይነት ስዩም መስፍን የሚመሩትና በእነስዩም በረደድ እና ሙሉጌታ አስራተ ናሳ አማንኝነት ሊካሄድ የታቀደው የወያኔ ሚሊኒየም በአል ለማክበር ይገኛሉ ከእኛ ጋር ያጨበጭባሉ ተብለው የተገመቱት ወገኖች ህሊና ሳይኖራቸው ቀርቶ ቢመጡ ሊያርፉበት የሚችሉትን ቤት ያለ ህዝብ ፍላጎት በአዲስ አበባ ህዝብ ትከሻ ላይ መቀመጥ የመረጡት የሞግዚቱ አስተዳደር ብርሃነ ዴሬሳ ፊርማ ወጪ የተደረገ ደብዳቤ ለከተማው ቤቶች ኤጀንሲ እንዲደርስ መደረጉ ታውቆዋል
በዚህም መሰረት ይህ ኢህአዴጋውያን የተጠራቀሙበት ኮሚነ የኮንዶሚኒየም ሕንፃዎችን ለመጠቀም ተፈቅዶለታል ሲሉ ምንጮቻችን ዘግበዋል
በዚሁ የወያኔ ሚሊኒየም በዓል እስከ 300 ሺህ የሚገመቱ እንግዶች ይመጣሉ የሚሉት እነስዩም በረደድ የግንቦቱን ምርጫ ተከትሎ ወያኔ ሰላማዊ ዜጎችን ሲገድል በእንባ እየተራጩ ወገኔ አለቀ አስጥሉልኝ ብለው ምእራባውያንና አውሮፓውያንን የተማጸኑ ዜጎች በወቅቱ የተቀረጸ ምስላቸው የተቃውሞ ድበጻቸውን ካሰሙበት አገር ከሚገኝ ኤምባሲ በወያኔ ኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚዎቸር ተቀነባብሮ አዲስ አበባ ለሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስነር መስሪያቤት መላኩንና የሚኒስነር መስሪያቤቱ የተለያዩ ክፍሎችና ዳይሬክቶሬቶች ውስጥ ያሉ የኢህአዴግ ታማኝ አገልጋዮች «እገሌ ፤ እገሌ» እያሉ በመምረጥ ላይ መሆናቸው ለማወቅተችሎዋል
ይህ የሚያገለግለው የሰው ዘር ማየት ያስጠላው ወያኔ ኢህአዴግ በአል ብለው የሚመጡ እንግዶችን ከቦሌ አየር ማረፊያ የእግረ ሙቅ በማጥለቅ አቀባበል ሊያደርግላቸው በማሰቡ መሆኑን ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስራ የበዛባቸው የደህንነት ተቁዋሙ ባልደረቦች መናገራቸው በዘገባው ተመልክቶዋል
ለበዓሉ የሚመጡትን እንግዶች ከሆቴሎች ሌላ ሌሎች ማረፊያ ቦታዎችን ለማመቻቸት ከሚያስችለው ዝግጅት አንዱ የሆነውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝግቦና ገንዘቡን ከፍሎ እረከባለሁ በማለት ከሚጠባበቀው ህዝብ በመንጠቅ ለመስጠት ስምምነት ላይ መደረሱን የሰሙ ወገኖች ጥራት የጎደለው እና በመሰነጣጠቅ ገና ከጅምሩ የማስመሰያ ግንባታ እንደነበረ ህዝቡ አውቆታል ከዚሁ ብሶ በሸፍጥ ለሌላ በማዛወር ገንዘብ ለማግበስበስ መሞከር አልጠግብ ባይነት ነው ሲሉ የወያኔ ኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናትን በሆዳቸው መሸነፍ አስመልክተው መተቸታቸው በዘገባው ተመልክቶዋል
እነስዩም በረደድ በበዓሉ ዋዜማ ዓመቱን በመሉ ሊመጡ የሚችሉ እንግዶችን በአዲስ አበባ ከተማ በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ኮንዶሚንየም ቤቶችውስጥ እንዲያርፉ በማድረግ የገቢ ምንጭ የሚሆኑበት መንገድ ተሰልቶ ስለሚገኘው ትርፍ ግምታዊ ስሌት የሚያሰላ ቡድን እንዶቁዋቁዋም ማድረጋቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ንን ዘገባ እያጠናቀርን ባለንበት ወቅት በተገኛ ተመሳሳይ የምንጮቻችችን ዘገባ በኮንዶሚኒየም ቤቶች ከሚያርፉ እንግዶች ሌላ በእነሱም መካከል ልዩነት በመፍጠር በኮንዶሚኒየም ለመቆየት የሚጠየቁት ክፍያ መክፈል ካልቻሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት ተማሪዎች ትምህርት እንዲያቆሙ ማድረግ አስቸጋሪ ነው ተብሎ ቢታሰብም ማደሪያ ክፍሎቻቸውን እንዲለቁ እና ዩኒቨርስቲዎች የመኝታ አገልግሎታቸውን ለእንግዳ ማረፊያ እንዲከራይ ሀሳብ መቅረቡን ለማወቅ ተችሎዋል
ይህ ሃሳብ ሁለት ዋና ዋና የተባሉ ጥያዎችን አስነስተው ነበር ያሉት ምንጮቻችን አንዱ የዩኒቨርስቲ መኝታዎች የሚያስገኙትን ገቢ በባለቤትነት የሚወስደው ማንነው᐀ የሚለው ሲሆን ሁለተኛው የክፍለሃገር ተማሪዎችን በተመለከተ ወዴት ማዘዋወር ይቻላል᐀ የሚለውን ከሌሎች ጥያቄዎች ጋር አዛምዶ መልስ ለመፈለግ ጉዳዩ ይጠና መባሉን ከታማኝ ውስጥ አዋቂ ለማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ዘግበዋል
በግቦት ወር 1997 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በማግኘት ከንቲባው እንዲሆኑለት ህዝቡ የመረጣቸውን ከንቲባ ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ወህኒ እንሰዲገቡ ያደረገው ወያኔ ኢህአዴግ ያለ ህዝብ ድጋፍ የሞግዚት አስተዳደር አድርጎ የመደባቸው ብርሃኑ ዴሬሳ እያወቁ የፍርደስ ቤት ውሳኔ መሻራቸው አዲስ አበባ የሚገኙ ምንጮች አስታወቁ
በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የከተማ ትርፍ ቤቶችን እንዲወረሱ ያደረገው የየካቲት 67 አዋጅ መሰረት ለረጅም ዓመታት የቀበሌ ናቸው በማለት ሲያከራክር የነበረውን ሁለት መኖሪያ ቤቶች በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ ብርሃኑ ዴሬሳና የበታች ሹማምንቶቻው መሻራቸው አነጋጋ መሆኑ ታዉቆዋል
አምና በሐምሌ ወር 1998 ዓ.ም. ለህጋዊ ወራሾች ይመለስ ሲል የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማው ሽሮታል ያሉት ምንጮች የወራሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ መሰረዝ በክፍለከተማው ቀበሌ 19/20 የሚገኙ የቤት ቁጥራቸው 130 እና 131 የሆኑ በ3.000 ካሬ ሜትር ላይ የተሰሩ ቤቶች በውርስ የተላለፈላቸው እና የቤቶቹ ባለቤት ስለመሆናቸውም የሚያረጋግጥ የማረጋገጫ ደብተር ያላቸው ወራሽ ከፍርድ ቤት የተወሰነላቸውን ውሳኔ ለመሻር የሚያበቃ ስልጣን እንደሌለው የህግ ባለሙያዎች መናገራቸውን ጨምረው አስረድተዋል
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቤቶቹ ላይ የባለቤትነት መብት ሳይኖረው በማከራየት ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱ እንዳለሆኖ ቤቶቹን እንዲያስረክብ ቢጠየቅም እምቢ ብሎዋል
ከሳሽ ክሱን ሲመሰርቱ ካቀረቧቸው ማስረጃ መካከል የቤቶቹ ባለቤት ስለመሆናቸውና በውርስ መተላለፋቸውን የሚያስረዳ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1985 ዓም የተሰጣቸውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ፍ/ቤቱ በማስረጃነት በመያዝ ፍ/ቤቱ ቤቶቹን ለከሳሽ እንዲያስረክቡ በ17/11/98 ዓ.ም. በመወሰን ለክፍለ ከተማው ያስታውቃል ፡፡
ይሁን እንጂ የፍ/ባለመብት ውሣኔው ተግባራዊ እንዳልሆነላቸው በመግለፅ ፍ/ቤቱ እንዲያስፈፅምላቸው በጠየቁት መሠረት በ10/2/99 ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
ቤቶቹ በፍርድ ባለእዳዎች ተይዘው ከሆነ በማስለቀቅ፣ ተቆልፈው ከሆነ በጥንቃቄ በመስበር ለፍፍርድ ባለመብት እንዲተላለፉ ለፖሊስ በትዕዛዝ ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ይህም ተግባራዊ እንዳይሆን ክፍለ ከተማው ያግዳል የዚህ ምክንየት ደግሞ ኢህአዴግ ታማኝ ባለሙዋሎች ጌቶቻቸውን የሚያስደስት የሚመስላቸው ህዝብን በማስለቀሳቸው እንደሆነ ስለሚያምኑ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጭራሹኑ ፍርድ ቤት የፃፈው ደብዳቤ ተቀባይነት እንደማይኖረው ለፍርድ ባለመብት እንዲያውቁት አደረገ፡፡
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ባለስልጣን ለክፍለ ከተማው በፃፈው ደብዳቤ ቤቶቹ ኪራይ የሚከፈልባቸው የመንግስት ቤቶች መሆናቸውን የሚያስረዳ መረጃ በማዕከል እንዳለ መግለፁን ክፍለ ከተማለው ደግሞ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን በሕገ ወጥ መንገድ የተሰጠን የበት ባለቤትነት ሥልጣን በሕገወጥ መንገድ የተሰጠን የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር መሠረዝ የሚችል ስልጣን ስላለው የፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኙ ባለመብቶች በእጃቸው የሚገኘውን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እንዲመልሱ መጠየቁ የአስተዳደር ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን ነጻ ነው እየተባለ የሚለፈፍለት ፍርድ ቤት በኢህዴግ ታማኝ አገልጋዮች የእጅ መዳፈ ላይ ያለ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ አንድ የህግ ባለሙያ መናገራቸው ታውቆዋል
ይህ ሁሉ ሲሆን በህዝብ ሳይመረጡ የተሾሙት ብርሃኑ ዴሬሳና ካቢኔያቸው ስለጉዳዩ እያወቁ ዝምታን መምረጣቸው የራሳቸውና የአባላቶቻቸው ጥቅም እስንልተነካ ድረስ ስለሌላው የህብረተሰብ ክፍል ምንም ደንታ የሌላቸው መሆኑን አስመስክሮዋል
በታቃዋሚነታቸው ስመጥር የሆኑ በሐገር ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች እንደ ጠላት የሚታዩበትና ሕልውናቸው በስጋትና በአደጋ ላይ እየወደቀ የመምጣቱን ጉዳይ ከቀን ቀን ድርጊቶች ገሐድ እያወጡት በሚጉኙበት ሒደት ላይ እንገኛለን፡፡
በመንግስት ከፍተኛ የኃላፊነት የሥልጣን እርከን የነበሩና ታማኝነታቸው አጠራጥሮ ከነበሩበት ቦታ ዝቅ ተደርገው ከተቀመጡት ግለሰቦች ጀምሮ ሕወሓትንና በኋላም ኢህአዴግን ትናንትም ሆነ ዛሬ በመቃወም በአደባባይ እስከማውገዝ በደረሱ ግለሰቦች ሕይወት ዙሪያ የሚፈፀመው ወንጀል አሳዛኝና አስገራሚ ከመሆን አልፎ የተፈፀመባቸው የግድያ ወንጀልም ሆነ የአሟሟታቸው ጉዳይ ሁኔታዎች ከሚጠቁሙት ውጭ ይህ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍር መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡
ይባስ ብለው « ግለሰቡ እራሱን በራሱ ገደለ፡፡» ደመኛ ገደለው «ወንጀል ፈፅሞ ሲያመልጥ ተገደለ» የሚሉ እና ሌላ ሌላም ሽፋን ሲሰጣቸው ይስተዋላል፡፡ ይህ አባባል የግድያውን ስልታዊነት የሚጠቁም እንደሆነ አንዳንድ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
በሰሜን ጎንደር የተገደለው ወጣት የሽምቅ ውጊያ መሪ አገዳደሉ የክልሉ ባለስልጣኖች እንደሚሉት «በደመኛ» ሳይሆን ሆን ተብሎ በተጠነሰሰ የባለጊዜዎች ሴራ እንደተገደለ አብዛኛው የክልሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
ቀኑ ሐሙስ ነው ወሩ መፊቢት 5 ቀን ከዛሬ 14 አመት በፊት 1985 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡45 አካባቢ በአድርቃይ ወረዳ በዛሪማ ከተማ አሳዛኝ የግድያ ወንጀል በወጣቱ የጦር መሪ በኪዳነ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር ላይ ተፈፀመ፡፡ በኪዳነማርያም ላይ የተፈፀመውን ግድያ አሰቃቂ የሚያደርገው በበርካታ ሽማግሌዎች ልመና በምህረት ከገባ ከአምስት ወር በኋላ በታዩት ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በተሰላ ደባ የሞት ሰላባ መሆኑ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ኪዳነማርያምና የተወሰኑ ጓደኞቹ በምህረት እንዲገቡ የመንግስት ባለስልጣኖች ሽማግሌዎችን በመላክ ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ በኋላ ከሃያ የማያንሱ ካህናትና ሸማግሌዎች የየአድባራቱን መስቀል በመያዝ አርማዛሊ ከተባለ በረሐ ዳር በአርማዶጋ ውስጥ ከሚገኙት ከእነ ኪዳነማርያም ጋር ጥር 10/1985 ዓም በመገናኘት ድርድር ተጀመረ፡፡
ብዙም ሳይቆዩ ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡ በዚህን ጊዜ ኪዳነና ጓደኞቹ ጦሩን ሰብስበው «በምህረት ልንገባ ነው» በማለት በተናገሩ ጊዜ ተቃውሞ ቢያጋጥማቸው ሁኔታውን ለማሳመን ሞክረው ነበር፡፡ በመጨረሻም ጦሩ «እንደሚገሏችሁ አትጠራጠሩ፡፡ እኛ ግን አንገባም፣ ደህና ሁኑ» በማለት ነበር የተሰናበታቸው ፡፡ አንዳንድ የጦሩ አባላት በኪዳነ ማርያም እግር እየወደቁ «ማማዬ ምነው ጥለኸን አትሂድ እንጂ᐀» እያሉ ቢለምኑትም የዋህ እንደሆነ የሚነገርለት ኪዳነማርያም ልቡ ጨክኖ « የሐገሬውን ሸማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶችን አላሳፍርም፣ አላሳዝንም እናንተ እዘኑ እንጂ» በማለት ነበር እንደ እናት የሚያዩትንና እንደ ልጅ የሚያየውን ጦሩን ጥሎ በምህረት የገባው፡፡
ኪዳነና ጓደኞቹ በተጠቀሰው ቀን በሙሉ ምህረት በዘሪማ ከተማ ቢገቡም፣ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ በመገኘት «በግል ያጠፋሁት ጥፋት ካለና የገደልኩት ካለ በሽማግሌ አማካኝነት የተፈረደብኝን እከፍላለሁ» በማለት ቃል ገብቷል፡፡ ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ቃል እንደገቡ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን በክልሉ ከሕወሓት ጋርና በኋላም ከኢህአዴግ በመወገናቸው ሲዋጓቸው የነበሩና የቤተሰቦቻቸውን ሐብት ንብረት ያወደሙና የነጠቁ ታጣቂዎች በአሁን ወቅት በስልጣን ላይ በመሆናቸው በኪዳነ ጓደኛ ላይ የማቁሰል አደጋ በማድረስና በማሰር ከፍተኛ በደልን በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ ሲረዳ ሐዘን ገብቶት እንደነበርና «እኔን አምነው እንዲህ ተሰቃዩ» በማለት ይቆጭ እንደነበርና እርሱም ሆነ ሌሎች ጓደኞቹ የወቅቱን ፖለቲካ ሲየጤኑትና ነገሮችን ሲመለከቷቸው የከተማው ኑሮ አልዋጥ ብሏቸው እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ ይናገራሉ፡፡
ኪዳነ ማርያም ከቤቱ በር ላይ ሲገደል በቅርብ የነበሩት መጠጥ በመሸጥ የሚተዳደሩት ወ/ሮ እንባ እየተናነቃቸው «ከእርሱ ጋር ሙሉ ምህረት ተደርጐለት በገባው ጉዋደኛው መታሰር ያበሳጨው ስለነበር ወዲያ ወዲህ ብሎ ነገሮችን ካስተካከለ በኋላ ሐሙስ ግንቦት 5 ቀን ጠዋት ጀምሮ ከሳሾቹንና ሽማግሌዎችን በመያዝ እስከ ሰባት ሰዓት እርቅ ሲያደርግ ውሎ በመጨረሻ ተሳካለት፡፡
ያን ቀን እቤት ሲገባ ደስተኛ ነበር፡፡ ምሳ በልቶ ወደ አድርቃይ ጉዋደኛውን ለማስፈታት እንደሚሄድ ነግሮኝ ከቤት ወጣ አሉ እንባቸውን አብሰው የዚያን ግዜውን ድርጊት አስታወሱና ቀጠሉ
«ከዚያም ዘጠኝ ሰዓት ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ከሐገሩ ሰዎችና ከአድርቃይ ምክር ቤት አባል ጋር ተመልሶ መጣ፡፡ ምነው ብዬ ብጠይቀው አንድ የሚያስጨርሰው ጉዳይ ስላለ ጉዞውን መሰረዙን ከነገረኝ በኋላ በጣም ሙቀት ስለነበር ሁሉም እበር ላይ ተቀምጠው ጠላ በማስመጣትና በመጠጣት ሲጫወቱ አመሹ፡፡ ኪዳነ አይጠጣም፣ ብቻ በእርቁ መደሰቱን ለመጣው ሁሉ ይናገራል፡፡ ሁለት ሰዓት ሲል ወደ ቤት ውስጥ ገቡ ትንሽ እንደቆዩም እራት አቅርቤላቸው በሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ስለሄዱ የቀሩት ትንሽ ነበሩ፡፡ ሶስት ሰዓት አካባቢ የአድርቃይ ም/ቤት አባል አቶ መለስ ይልማ ተሰናብተውን ወጥተው ሄዱ፡፡ ልክ እርሳቸው እንደወጡ ሁለት የደደቢት ጦር ሠራዊት አባላት ወደቤት ገቡ፡፡ መሣሪያ ይዘዋል፡፡ የቀሩት ኪዳነና አብሮ አደግ ጓደኛው ነበሩ፡፡ እርሱም 3፡20 ሲል ተሰናብቶን ወደቤቱ ሄደ፡፡ ለተጋዮች ቢራ አቅርቤላቸው ይጠጣሉ፡፡
«በወሬ ወሬ ኪዳነና ታጋዮች ይጨዋወቱ ጀመር፡፡ የሚነጋገሩት በትግርኛ በመሆኑ ምን እንደሚሉ አልሰማም፡፡ ብቻ ከኪዳነ ፊት ላይ የመበሳጨትና የቁጣ ስሜት ይታይበት ነበር፡፡ ፊቱ ሲለዋወጥ ይታየኛል፡፡ ታጋዮች ሒሳብ ከፍለውኝ ሲወጡ አንዱ በሰላም እደሩ ብሎን ሲሄድ ሌላው ዝም ብሎን ወጣ፡፡
3፡45 ይል ነበር ሰዓቴ፡፡ ወዲያውኑ ኪዳነ እነርሱ ሳይርቁ ሽንቴን ሸንቼ ልምጣ በማለት ወጣ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የአውቶማቲክ ጥይት ድምፅ ተሰማ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ ተደናግጠን ስንወጣ ኪዳነ በግንባሩ ተደፍቶ ወድቋል» በማለት ሲቃ እየተናነቃቸውና እያለቀሱ እማኝነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በእለቱ የደረሰላቸው የፀጥታ ኃይልም ሆነ የቀበሌ ጠባቂ እንዳልነበረ በምሬት የገለፁት ወ/ሮዋ «ሌላው ቀርቶ» ይላሉ «ሌላው ቀርቶ ከቤት ሲጠጡ ያመሹት ታጋዮች እንኳ ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ወደ እኛ ቀርበው ሁኔታውን ከማጣራት ይልቅ ከጎረቤት በር ተቀምጠው ሰው ወደ እኛ እንዳይጠጋ ይከለክሉ እንደነበር አምልጠዋቸው የመጡ ሴት ጎረቤታችን ነግረውናል፡፡ ወንዶችን ግን በጭራሽ አላሳለፏቸውም በማለት ስለ ያንግዜው ያስረዳሉ፡፡
ሌላው አሳዛኝና አስተዛዛቢ ድርጊት ሬሳ አንስተን እቤት ካስገባን በኋላ እንኳን ማንም የመንግስት ኃይል ሳይደርስልን ጡሩንባ እየተነፋ «በአካባቢያችን ችግር በመፈጠሩ ማንም ሰው ከ12 ሰዓት በፊት እንዳይወጣ » ተብሎ የመለፈፉ ጉዳይ ነው፡፡ ድርጊቱን ማለትም ግድያውን ቀበሌው ቀደም ብሎ ያውቅ ነበር በማለት እንድንጠራጠር ተገደናል፡፡ ይህንንም የሚያጎለብተው በርካታ ታጣቂዎችና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሚገኙበት ሁኔታ ማን ነው ይህን መሰል ግድያ የሚፈፅም᐀ ግድ ያው ከተፈፀመ በኋላስ ተኩስ ሲሰማ እንዴት አንድ ሐይል ዝር ብሎ አልጠየቀንም᐀ ከዚህ በፊት ግን በተመሣሣይ ሰዓት እንኳን ጥይት ተተኩሶ ሰው በዱላ ተደብድቦ ተገደለ ሲባል በቦታው በመገኘት ተጠርጣሪዎችን ጓዳ ድረስ እየገቡ የያዙ ሐይሎች ምነዋ በዚህች ቀን አልደረሱልንም᐀ ይህንን ስንመለከት በግድያው ላይ የአካባቢው ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበት ልንጠረጥር ችለናል፡፡ ኪዳነም ቢሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ «ገዳዮቼ እናንተ ናችሁ፣ ከሐገሬ ሰው ጋርስ ነገርም የለኝ» እያለ ይነግራቸው እነደነበር እነርሱም ሲያዩት ጥሩ አመለካከት እንደሌላቸው አስታውሳለሁ፡፡ በማለት በንዴትና በቁጭት የሚያጫውቱት የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው
በሐዘን የተጎዳ ፊታቸውን ቅጭም እንዳደረጉ እኛም በማያፀብሪ በአድርቃይና በዛሪማ ከተማ ተዘዋውረን ኪዳነ ከገጠር ሕይወት እስከ ጦር መሪነት ያለውን እቅስቃሴና እንዴት ወደ ጠንካራና ተዋጊነት ሕይወት ሊገባ እንደቻለ ዘመድ አዝማድ ጓደኞቹ ሲማገሩ «ደፋርና ቀልጣፋ ሆኖ ከሕፃንነቱ ጀምሮ ያደገው ኪዳነ ማርያም ከቤተሰቦቹ ጋር በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርቶ እያለ አንድ የፖለቲካ ሹም በእርሱና በአካባቢው ነዋሪ ላይ ያደርግ የነበረውን ተፅእኖ በትዕግስት ይቀበል ዘንድ ግድ ሆነበት፡፡ አንድ ቀን ነገሮች ሁሉ እንደማይስተካከሉ ግን ያልማል፡፡ ከቀን ቀን ግለሰቡ የሚያደርገው ተፅእኖ አማረረውና የአባቱን ጠበንጃ አንስቶ ሰውየውን ከገደለ በኋላ መሣሪያውን በመያዝ ነበር የትውልድ ቀየውን ጠለምት ወረዳ ልዩ ስሟ መንታ ዲማራ የተባለችውን ለቆ በሰሬንታ በረሐ የአመፅ ውሎን የጀመረው፡፡
ይህ የሆነው በ160ዎቹ ውስጥ ነበር፡፡ኪዳነ ማርያም ገና ከጅምሩ ይህ ነው በማይባል በርካታ ፈተናዎች ተጋረጠበት፡፡ በተከዜ በረሐ ወርዶ ለደርግ ከነመሣሪያው እጁን በሰጠ ማግስት ወደ ጎንደር ወህኒ ቤት ተወረወረ፡፡ ከወህኒ ቤት ወደ ግድያ ቦታው ወደ ደባርቅ በመኪና ተጭነው ሲሄዱ ሌሎች እስረኞችን በማስተባበር ከመኪና ዘለው ሲወርዱ የጥይት እሩምታ ወረደባቸው፡፡ እንደምንም ተንከባለው አመለጡ፡፡
ከዚያም በተለያዩ የሰሜን ጎንደር ክለሎች እየተዘዋወረ የራሱን እንቅስቃሴ በማድረግና እያደፈጠ የደርግን ሠራዊት ያጠቃ ጀመር፡፡
ኢህአዴግ ጎንደር ከተማን ሊቆጣጠር እየገሰገሰ ሲመጣ ለስንት ቀናት ያህል በከተማው ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የመከላከል ተግባርን ካከናወኑ በኋላ ኪዳነና የሽምቅ ጦር አባላት የሁኔታውን መበላሸት በማጤን ስልታዊ ሽሽት በማድረግ ወደለመዱት በረሃ ገቡ፡፡ ኢህአዴግ ጐንደርን ተቆጣጠረ፡፡
ከዚያም በኋላ በሰሜን ጐንደር ክልል በአርማደጋ፣ በጠለምት መሐልና በተከዜ ዳርዳር፣ በአርማጭሆ፣ በማያፀብሪ፣ በብራ፣ በዳንሻና በመሳሰሉት በረሐዎች እየተንቀሳቀሱ የኢህአዴግን ጦር በተደጋጋሚ የገጠሙ ሲሆን በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚገኙትን ሌቦችና ነፍስ ገዳዮችን በመያዝ የሕዝቡን ሰላም ያስጠብቁ እንደነበር የአድርቃይ ገበያተኞች ምስክር ናቸው
ኪዳነ ይመራው በነበረው ጦር ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ ለሩህ ሩህነቱ «ማማዬ» የሚል ስም ሲወጣለት ለጥንካሬውና ለጦር ባለሟልነቱ ደግሞ «ኦራል» እያለ ይጠሩት ነበር፡፡ (ኦራል የከባድ መኪና ስም ነው)
በሌላ መልኩ የሰሜን ጐንደር አስተዳደር ባለሥልጣኖች ስለ ኪዳነ ማርያም «ኪዳነ ቀማኛና ዘራፊ ሽፍታ ነበር» ነው ይበሉ እንጂ ይህ አባባል በአብዛኛው በተቃዋሚነት በተሰለፉ ከኢህአዴግ አካላት የሚሰነዘር እንጂ ኪዳነ ማሪያም የሕዝብ ፍቅር ያለው እንደነበር የሚገልፁ ብዙዎች ናቸው፡፡
ከዛሬ አስራ አራት አመት በፊት አርብ ግንቦት 6 ቀን 1985 ዓም ብዙ ሕዝብ በተገኘበት የኪዳነ ማርያም የቀብር ሥነ ሥርዓት በሱቋር ዋልድባ ኪዳነ ምህረት ከመፈፀሙ በፊት በምሕረት ካስገቡት ሽግማሌዎች አንዱ ሰው በተሰበሰበበት መሐል «እኛ ስናስገባው እንኳን ለመገደል ለመታሰር አልነበረም ያመጣናቸው፣ ከእንግዲህ በኋላ በኛ የገባችሁ የላችሁም መሐላም ፈርሷል» በማለት በምሬት እንደተናገሩ በለቅሶው ከተገኙ የአካባቢው ነዋሪዎችና የኪዳነ ቤተሰቦች ያስረዳሉ፡፡
ኪዳነ ማርያም ሲሞት የ37 ዓመት ጐልማሣና የሁለት ልጆች አባት ነበር፡፡በእነ ኪዳነ ሽምግልና ላይ የነበሩ አዛውንት «ወንዱን እጁን ይዘን ሰጠነው» ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል
የኪዳነ ማርያም የአሟሟት እንቆቅልሽ የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናት «ደመኛ ገደለው» በሚሉትና በአብዛኛው ኅብረተሰብ የሚወራው «በኢህአዴግ ታጣቂዎች አማካኝነት ባለፉት ዓመታት በርካታ የሕወኅት አባላትንና ባለሥልጣናትን በላውንቸር ደብድቦ ገድሎ ሐውልት በተሰራላቸው በዛሪማ ከተማ የበቀል እርምጃ ተወሰደበት» የሚለው ጥርጣሬ መካከል የሚገኝ እውነታ ይሆናል፡፡ ሁኔታውን አገናዝቦ ትክክለኛ ብይንን መስጠት ከተቻለ እንቅቆልሹ ይፈታል፡፡
ድንበር ዘለሉን ጦርነት ያለ ህዝብ ድጋፍ በራሱ ስሜት እየተነዳ ሠራዊቱን በጦርነት ሲማግድ የቆየው ወያኔ ኢህአዴግ በሞቃዲሾው ጦርነት አፈፃፀም ላይ ያለውን የውጊያ ውሎ በተመለከተ ግምገማ ላይ መሆኑን የመከላከያ ታማኝ ውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ ምንጮቻችችን ዘገቡ
በመከላከያ ሰራዊቱ አጠቃላይ የሞቃዲሾ ጦርነት ውሎን በተመለከተ ተሰራ የተባለውን አስመልክቶ በአዛዥነት ደረጃ ባሉ መኮንኖች ግምገማ መጀመሩንና በሃሳቦች ያለመግባባት ተጠናክሮ መታየቱ ዘገባው አመልክቶዋል
የመከላከያ ሰራዊቱ አፈፃፀሙ በጣም አጥጋቢ ነው ተብሎ የነበረ ቢሆንም በመጀመሪያ ደረጃ ወታደራዊ ብቃቱን ለሚፈታተኑ ተግባራት እንዲጋለጥ ሆኑዋል ለዚህም ያበቁት በአዛዥነት ላይ የነበሩ ናቸው የሚለው የግምገማ ውንጀላ ብዙዎችን አስኮርፉዋል
በተቀናጀ አኳኋን ሥራውን ፈፅሟል ለማለት አፍን ሞልቶ መናገር ያስቸግራል ያሉት ስብሰባውን ለመምራት በጄኔራል ሳሞራ የኑስ የተወከሉት የመድረኩ መሪ ንግግራቸው ተሳታፊዎችን አስቀይሞ እንደነበር ከዘገባው ለማወቅ ተችሎዋል
በሶማሊያ ሲቪል ህዝብ ላይ የተፈራውን ያክል ጉዳት እንዳይደርስ የተደረገው ጥሩ ነው ሊባል የሚችል ቢሆንም ጉዳቱ መድረሱ አልቀረም የዚህ ምክንያት የጠላት ከህዝቡ ጋር መመሳሰል እንደሆነ ታሳቢ በማድረግ የምናልፈው ቢሆንም ግን ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን ከአደጋ ለመከላከል እና ሪስክ ላለመውሰድ ሲባል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ማድረስ ከወታደራዊ ግዳጅ አይጠበቅም
ራስን ለመከላከል ሲባል በሲቪል ሰው ላይ የተወሰደው እርምጃ የሰራዊቱን ብቃት አነጋጋሪ ያደርገዋል በዚህ ዙሪያ ወደፊት በየደረጃው እያነሳን የምንገመግመው ይሆናል በማለት ከማስፈራራት ባልተናነሰ ሁኔታ ወታደራዊ መኮንኖቹን ሲያሸማቅቁ መሰንበታቸውን የመከላከያ ታማኝ ውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ ምንጮቻቻን ዘግበዋል
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአየር ሃይል የተደረገውን ድብደባ አስመልክቶ ተመሳሳይ ግምገማ መሄዱን ዘገባው አመልክቶዋል
በተለይ አየር ሃይልንና የጦርነቱን ውሎ አስመልክቶ በሱማሊያና በኬንያ ድንበር አቅራቢያ በተደረገ የአየር ድብደባ የተፈጸመው ስህተት ሳይሆን ሆን ብሎ የተደረገ እና የብቃት ማነስ ነው ተብሎ ከወያኔ ቱባ ወታደራዊ አዛዦች የቀረበው ውንጀላ በአየር ሀይል አባላት ውስጥ ለማባረርና ለመወንጀል የታሰበ ሴራ መኖሩን አመላንች ነው ሲሉ የጉዳዩ ተልካቾች መናገራቸው ተመልክቶዋል
ወታደራዊ ብቃትና ጀግንነት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ጉዳይ ቢሆንም በማእከል በሚሰጠው አመራር የተገኘ ስኬት እንጂ ሰራዊቱን በተመለከተ የነበረውን ዝርክርነት በየደረጃው ወደፊት የምናየው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በግዳጁ ወቅት የምስራቅ እዝ አንል ከሆነው ክፍለጦር አፍ አውጥቶ አንዋጋም እስከማለት የደረሱትን አባላት የመመንጠር ስራ ማከናወን አለብን ስለዚህ በየደረጃው በየክፍሉ እንዲህ ያለ አኩይ እንቅስቃሴ Cጠየደርጉ የነበሩትን የተመለከተ የስም ዝርዝር እንድታስተላልፉልን በማለት ለተሰብሳቢ ወታደራዊ መኮንኖችና አዛዦች መመሪያ መተላለፉን ያመለከተው የመከላከያ ታማኝ ውስጥ አዋቂዎችን የጠቀሰው የምንጮቻችን ዘገባ በቅርቡ በሶማሊያው ድንበር ዘለል ጦርነት የተካፈሉ የነበሩት የወያኔ ኢህአዴግ ሰራዊት አባላት እድላቸው ሆኖ ከሞት የተረፉት በግምገማ ሰበብ ተፈልጎላቸው ሊባረሩ እቅድ በመነደፍ ላይ መሆኑን በእርግጠኝነት አስረድተዋል

ራስን ለመከላከል ሲባል በሲቪል ሰው ላይ የተወሰደው እርምጃ የሰራዊቱን ብቃ/